ወላይታ ድቻ የግራ መስመር ተከላካይ ለማስፈረም ተስማማ

የአንደኛው ዙር አጋማሽ ላይ ተጫዋች ለማስፈረም እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ወላይታ ድቻ የግራ መስመር ተከላካይ ለማስፈረም ተስማምቷል።

ከዚህ ቀደም በደደቢት፣ ኢትዮጵያ ቡናና በሁለት አጋጣሚዎች በባህር ዳር ከተማ መጫወት የቻለው እና ባለፈው ዓመት በመቐለ 70 እንደርታ ያሳለፈው ታታሪው የግራ መስመር ተከላካይ አስናቀ ሞገስ ለወላይታ ድቻ ለመጫወት ቅድመ ስምምነት ፊርማውን አኑሯል። የአንደኛው ዙር ተጠናቆ የዝውውር መስኮቱ ሲከፈት በፌዴሬሽን ውሉ እንደሚፀድቅም ይጠበቃል።

በውድድር ዓመቱ ሁነኛ የግራ ተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ፍለጋ በርካታ ተጫዋቾችን በቦታው አፈራርቆ ለተጠቀመው ድቻ የአስናቀ ሞገስ ዝውውር እንደ መልካም ዜና የሚቆጠር ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ