“…እህቴ የልጅ እናት መሆኗን ለመግለፅ ነው” – ሚኪያስ መኮንን

ከጉዳት መልስ ወደ ትክክለኛው አቋሙ ለመመለስ እየጣረ የሚገኘው ወጣቱ የመስመር አጥቂ ሚኪያስ መኮንን አስደናቂውን ጎል ካስቆጠረ በኃላ ደስታውን ስለገለፀበት መንገድ ይናገራል።

በሊጉ ያለፉትን ዓመታት ካየናቸው በፈጠራ ብቃት እናቴክኒክ ችሎታ የታደሉ ተጫዋቾች መካከል የሚመደበው ሚኪያስ መኮንን በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመርያዎቹ ሳምንታት የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረግ ቢችልም ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ ባጋጠመው ጉዳት ለሳምንታት ከሜዳ ከራቀ በኃላ ባሳለፍነው ሳምንት ከወላይታ ድቻ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ተቀይሮ በመግባት ጥሩ መንቀሳቀስ ችሎ ነበር። በዛሬው ዕለትም ወደ መጀመርያ አሰላለፍ በመግባት እጅግ አስገራሚ የሆነ ጎል አስቆጥሯል። ሚኪያስ ጎል ካስቆጠረ በኃላ ኳስ. በሆዱ አድርጎ ደስታውን የገለፀበት መንገድ እና ጎሉን ያስቆጠረበትን ሒደት አስመልክቶ አናግረነዋል።

” ኳሱን በእንቅስቃሴ ካለፍኩ በኃላ የግብጠባቂውን አቋቋም አይቼ ነው ጥሩ ጎል ማስቆጠር የቻልኩት። በዚህም በጣም ደስ ብሎኛል። ጎሎኑ አግብቼ ደስታዬን የገለፅኩት ታላቅ እህቴ በትናንትናው ዕለት የወንድ ልጅ እናት በመሆኗ እሱን ለመግለፅ እና ለማሰብ ፈልጌ ነው በዚህ መልኩ የገለፅኩት።

“ያለፉትን ሳምንታት የደረሰብኝ ጉዳት ከጨዋታ መራቄ የአካል ብቃት ዝግጁነት ላይ ተፅእኖ አድርጎብኛል። ባለፈው ተቀይሬ በመግባት መጫወት ችያለው። ዛሬ ደግሞ ወደ መጀመርያ አሰላለፍ በመግባት ለመጫወት ችያለው። አሁን ወደ ትክክለኛው እንቅስቃሴ በመግባት ኢትዮጵያ ቡናን ለማገልገል አስባለሁ።”


© ሶከር ኢትዮጵያ