ሀዋሳ ከተማ ከ አዳማ ከተማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

ረፋድ ላይ የሚካሄደው የአዳማ እና የሀዋሳ ጨዋታ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።

ብዙ የተለየ ዝግጅት ባያደርጉም እንደእስካሁኑ በ 4-3-3 የተጨዋቾች አደራደር ተጠቅመው እንደሚጫወቱ እና መጠነኛ የተጫዋቾች ለውጥ ማድረጋቸውን የተናገሩት አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ያለግብ ከተለያዩበት ጨዋታ ሦስት ለውጦችን አድርገዋል። በለውጦቹ አዲስዓለም ተስፋዬ ፣ ጂብሪል አህመድ እና ሄኖክ ድልቢ ወደ መጀመሪያ አሰላለፍ ሲመጡ ዳንኤል ደርቤ ዳዊት ታደሰ እና ኤፍሬም ዘካርያስ ከቀዳሞው አሰላለፍ ውጪ ሆነዋል።

አዳማ ከተማ በድሬዳዋ ከተሸነፈበት ጨዋታ ግብ ጠባቂ ቦታ ላይ ኢብሳ አበበን በታሪክ ጌትነት ሲተካ ከጉዳት የተመለሰው ታፈሰ ሰርካ እና አካሉ አበራ የእዮብ ማቲዮስ እና ብሩክ ቦጋለን የመስመር ተከላካይነት ሚና ተረክበዋል። በሌሎች ለውጦች ጉዳት የገጠመው አምበሉ የኋላሸት ፍቃዱ እና ዘሪሁን ብርሀኑ በፍሰሀ ቶማስ እና ቴውድሮስ ገብረእግዚያብሄር ተተክተዋል። አሰልጣኝ አስቻለው ኃይለሚካኤል እንደሁል ጊዜው ስህተቶቻቸውን አርመው ለመቅረብ ጥረት እንዳደረጉ እና ከሌላው ጊዜ በተለየ ቡድናቸው በአንድ ተከላካይ አማካይ እንደሚገባ ገልፀዋል።

ጨዋታውን ዓለምአየሁ ለገሰ በዋና ዳኝነት ይመሩታል።
ሀዋሳ ከተማ

1 ሜንሳህ ሶሆሆ
6 አዲስዓለም ተስፋዬ
4 ምኞት ደበበ
26 ላውረንስ ላርቴ
12 ደስታ ዮሐንስ
5 ጋብሬል አህመድ
25 ሄኖክ ድልቢ
29 ወንድምአገኝ ኃይሉ
21 ኤፍሬም አሻሞ
17 ብሩክ በየነ
10 መስፍን ታፈሰ

አዳማ ከተማ

23 ታሩክ ጌትነት
13 ታፈሰ ሰርካ
20 ደስታ ጊቻሞ
44 ትዕግስቱ አበራ
3 አካሉ አበራ
22 ደሳለኝ ደባሽ
12 ቴዎድሮስ ገብረእግዚአብሄር
9 በላይ ዓባይነህ
8 በቃሉ ገነነ
7 ፍሰሀ ቶማስ
10 አብዲሳ ጀማል

©ሶከር ኢትዮጵያ