ሀዲያ ሆሳዕና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

የ11ኛውን ሳምንት ቀዳሚ ጨዋታ የተመለከቱ የመጨረሻ መረጃዎችን እነሆ።

አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ በአስረኛው ሳምንት ከሰበታ ከተማ ጋር ካደረጉት ጨዋታ በኋላ ቡድኑ ልምምድ ሳያደርግ ለዛሬ ጨዋታ መቅረቡ ተፅዕኖ እንደሚያደርግባቸው ገልፀዋል። ሆሳዕና ያለ ግብ ከተለያየበት የሰበታው ጨዋታ አሰላለፍ ውስጥ ሦስት ቅያሪዎችን አድርጓል። አዲስ ህንፃ ፣ አልሀሰን ካሉሻ እና ሚካኤል ጆርጅ ወደ መጀመሪያ አሰላለፍ ሲመጡ ባልተጠበቀ ሁኔታ ሄኖክ አርፌጮ ፣ ዳዋ ሆቴሳ ፣ ሳሊፍ ፎፋና ጨዋታውን አልጀመሩም።

ክለቡ ትናንት ስለወሰናቸው ውሳኔዎች ብዙ ማለት እንደማይፈልጉ እና ትኩረታቸው በዛሬው ጨዋታ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ መሆኑን የተናገሩት አሰልጣኝ ማሂር ዴቪድስ ከሲዳማ ቡና አቻ ሲለያዩ የተጠቀሙበትን አሰላለፍ ሳይለውጡ ቀርበዋል።

ጨዋታውን ፌደራል ዳኛ አዳነ ወርቁ በመሀል ዳኝነት ይመሩታል።

የሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

ሀዲያ ሆሳዕና

77 መሐመድ ሙንታሪ
2 ሱሌይማን ሀሚድ
5 አይዛክ ኢሴንዴ
25 ተስፋዬ በቀለ
3 ቴዎድሮስ በቀለ
23 አዲስ ህንፃ
13 አልሀሰን ካሉሻ
10 አማኑኤል ጎበና
14 መድኃኔ ብርሀኔ
22 ቢስማርክ አፒያ
11 ሚካኤል ጆርጅ

ቅዱስ ጊዮርጊስ

1 ለዓለም ብርሀኑ
14 ሄኖክ አዱኛ
3 አማኑኤል ተርፋ
24 ኤድዊን ፍሪምፖንግ
6 ደስታ ደሙ
26 ናትናኤል ዘለቀ
5 ሀይደር ሸረፋ
17 አዲስ ግደይ
10 አቤል ያለው
28 አማኑኤል ገብረሚካኤል
9 ጌታነህ ከበደ


© ሶከር ኢትዮጵያ