ሁለገቡ ተጫዋች ወደ ነብሮቹ አምርቷል

ሁለገቡ ተጫዋች ወደ ነብሮቹ አምርቷል

በመቐለ 70 እንድርታ ቆይታ የነበረው ተጫዋች ለሀድያ ሆሳዕና ለመጫወት ተስማማምል።

ሀድያ ሆሳዕናዎች በዝውውሩ የነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል ከማራዘም ባሻገር ቢንያም ጌታቸው ፣ ወንድማገኝ ማዕረግ፣ ኢዮብ ገብረማርያም ፣ ብርሀኑ አዳሙ፣ ያሬድ ታደሰ እና ቶሎሳ ንጉሴን ማስፈረማቸው ይታወቃል። አሁን ደግሞ ሁለገቡን ተጫዋች አብዲ ዋበላን አስፈርመዋል። በአዳማ ከተማ የእግር ኳስ መነሻውን ያደረገው አብዲ ያለፉት ሁለት ዓመታት በምድረ ገነት ሽረ እና በመቐለ 70 እንድርታ ሲጫወት ቆይቶ አሁን ለሁለት ዓመት ለሀድያ ሆሳዕና ፊርማውን አኑሯል።