ሀዋሳ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

12ኛው ሳምንት የሚጠናቀቅበትን ጨዋታ የተመለከቱ መረጃዎችን እነሆ ብለናል።

አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ከወልቂጤ ጋር ነጥብ ከተጋሩበት ጨዋታ አንፃር ዛሬ ሁለት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም አለልኝ አዘነ እና ዮሐንስ ሴጌቦ የወንድምአገኝ ኃይሉ እና ዘነበ ከድርን ቦታ ሸፍነው ይጫወታሉ። በተሰረዘው የውድድር ዓመት ከፍተኛ ቅጣት ተጥሎት የነበረው አለልኝ አዘነም ከአንድ ዓመት የቅጣት ቆይታ በኋላ ዘደ ሜዳ ተመልሷል። ወጣቱ አሰልጣኝ የዕረፍቱ ጊዜ ተጨዋቾች እንዲያገግሙ እንዲሁም በቡድኑ ደካማ ጎን ላይ ለመስራት ጥሩ ዕድል እንደፈጠረላቸው ገልፀዋል።

ሁለንም ጨዋታ እንደ ፍፃሜ በማየት የሌሎቹን ውጤት ሳይጠብቁ የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው ለመወሰን ለማሸነፍ እንደሚገቡ የጠቀሱት አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ በድሬዳዋው ጨዋታ ከተጠቀሙበት አሰላለፍ ባደረጉት ብቸኛ ለውጥ ከቅጣት የተመለሰው ሱራፌል ዳኛቸውን በይሁን እንዳሻው ምትክ በመለወጥ ለዛሬው ጨዋታ ቀርበዋል።

ፌደራል ዳኛ አክሊሉ ደጋፌ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት እንዲመሩ ተመድበዋል።

ቡድኖቹ ዛሬ ጨዋታውን የሚጀምሩበት ስብስብ ይህንን ይመስላል።

ሀዋሳ ከተማ

1 ሜንሳህ ሶሆሆ
7 ዳንኤል ደርቤ
4 ምኞት ደበበ
26 ላውረንስ ላርቴ
19 ዮሐንስ ሴጌቦ
18 ዳዊት ታደሰ
23 አለልኝ አዘነ
3 ኤፍሬም ዘካርያስ
21 ኤፍሬም አሻሞ
17 ብሩክ በየነ
10 መስፍን ታፈሰ

ፋሲል ከነማ

1 ሚኬል ሳማኬ
2 እንየው ካሣሁን
5 ከድር ኩሊባሊ
16 ያሬድ ባየህ
21 አምሳሉ ጥላሁን
14 ሀብታሙ ተከስተ
10 ሱራፌል ዳኛቸው
17 በዛብህ መለዮ
7 በረከት ደስታ
19 ሽመክት ጉግሳ
26 ሙጂብ ቃሲም


© ሶከር ኢትዮጵያ