አዳማ ከተማ ከ ሰበታ ከተማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

ከጨዋታው መጀመር አስቀድሞ ልታውቋቸው የሚገቡ ነጥቦችን እንዲህ አዘጋጅተንላችኋል።

ከድል የተመለሱት አሰልጣኝ አስቻለው ኃይለሚካኤል የነበሩብንን ስህተቶች አርመን ያለፈውን ውጤት ለማስቀጠል እንገባለን ሲሉ ኃሳባቸውን የሰነዘሩ ሲሆን ከሰባት ሳምንታት በኃላ ወደ አሸናፊነት በተመለሱበት ስብስብ ላይ ምንም ለውጥ ሳያደርጉ ቀርበዋል።

የአጨዋወት ለውጥ አድርገን ከሌላው ጊዜ በተለየ ሙሉ ለሙሉ ማጥቃት ላይ እናተኩራለን ያሉት አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ በበኩላቸው ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ነጥብ በተጋሩበት ጨዋታ በተጠቀሙበት አሰላለፍ ላይ ያልታሰበ የስድስት ተጫዋቾች ለውጥ አድርገዋል። ቡድኑ ወደ አራት ተከላካይ መስመር ሲመለስ አለማየሁ ሙለታን በጌቱ ኃይለማርያም የለወጠ ሲሆን ዳዊት እስጢፋኖስ ፣ ታደለ መንገሻ ፣ ቃልኪዳን ገዛኸኝ ፣ ዱሬሳ ሹቢሳ እና ፍፁም ገብረማርያም ወደ መጀመሪያ አሰላለፍ ሲመጡ አለማየሁ ሙለታ ፣ አዲስ ተስፋዬ ፣ ኢብራሂም ከድር ፣ ቡልቻ ሹራ እና እስራኤል እሸቱ አርፈዋል።

ዳዊት እና ታደለ ከሳምንታት ጉዳት በኃላ ወደ ጨዋታ ተመልሰዋል።

ጨዋታውን ኃይለየሱስ ባዘዘው በመሀል ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል።

ሁለቱ ቡድኖች ይዘውት የሚገቡት አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

አዳማ ከተማ

23 ታሪክ ጌትነት
13 ታፈሰ ሰርካ
20 ደስታ ጊቻሞ
44 ትዕግስቱ አበራ
3 አካሉ አበራ
22 ደሳለኝ ደባሽ
12 ቴዎድሮስ ገብረእግዚአብሄር
9 በላይ ዓባይነህ
8 በቃሉ ገነነ
7 ፍሰሀ ቶማስ
10 አብዲሳ ጀማል

ሰበታ ከተማ

1 ምንተስኖት አሎ
5 ጌቱ ኃይለማርያም
4 አንተነህ ተስፋዬ
13 መሳይ ጳውሎስ
23 ኃይለሚካኤል አደፍርስ
10 ዳዊት እስጢፋኖስ
15 አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ
17 ታደለ መንገሻ
27 ዱሬሳ ሹቢሳ
16 ፍፁም ገብረማርያም
20 ቃልኪዳን ዘላለም

© ሶከር ኢትዮጵያ