አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ወላይታ ድቻ ከ ባህር ዳር ከተማ

ከደቂቃዎች በኋላ የሚጀምረውን ጨዋታ የተመለከቱ መረጃዎችን እነሆ።

እያንዳንዱ ጨዋታ ወሳኝ መሆኑን የገለፁት አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ከወራጅ ቀጠናው ከመራቅ በዘለለ ወደ ፉክክሩ ለመጠጋት ጥረት እንደሚያደርጉ እንዲሁም ዕረፍቱ ከጨዋታ ሰዓት ባለፈ ተጫዋቾቻቸው ያላቸውን አቅም ለመረዳት እንደጠቀማቸው ተናግረዋል። አሰልጣኙ ጅማን ከረቱበት ጨዋታ ባደረጓቸው ለውጦች ከቡድኑ በተቀነሰው ነጋሽ ታደሰ እና መልካሙ ቦጋለ ምትክ እንድሪስ ሰዒድ እና ቸርነት ጉግሳን አስጀምረዋል።

ወደ ከተማቸው እና ለጨዋታ አመቺ ወደሆነው ሜዳ በመመለሳቸው ደስ መሰኘታቸውን እና በዕረፍቱ ቀናት ቡድኑ ላይ የነበሩትን ችግሮች ለማስተካከል መስራታቸውን የታናገሩት አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ቡድናቸው ከጅማ አባ ጅፋር ጋር ነጥብ ሲጋራ ከተጠቀሙበት አሰላለፍ ውስጥ ሦስት ለውጦች ሲያደርጉ ግብ ጠባቂው ፂዮን መርዕድ በሀሪሰን ሄሱ ፣ ሳሙኤል ተስፋዬ በሚኪያስ ግርማ በረከት ጥጋቡ ደግሞ በፍቅረሚካኤል ዓለሙ ተተክተዋል።

ጨዋታውን ኢንተርናሽናል ዳኛ ለሚ ንጉሤ በመሀል ዳኝነት ይመሩታል።

የሁለቱ ቡድኖች አሰላለፍ ይህንን ይመስላል :-

ወላይታ ድቻ

99 መክብብ ደገፉ
9 ያሬድ ዳዊት
12 ደጉ ደበበ
26 አንተነህ ጉግሳ
16 አናጋው ባደግ
20 በረከት ወልዴ
8 እንድሪስ ሰዒድ
21 ቸርነት ጉግሳ
27 መሳይ አገኘሁ
4 ፀጋዬ ብርሀኑ
13 ቢኒያም ፍቅሩ

ባህር ዳር ከተማ

99 ሀሪሰን ሄሱ
3 ሚኪያስ ግርማ
15 ሰለሞን ወዴሳ
6 መናፍ ዐወል
13 አህመድ ረሺድ
21 ፍቅረሚካኤል ዓለሙ
24 አፈወርቅ ኃይሉ
18 ሳለአምላክ ተገኘ
14 ፍፁም ዓለሙ
10 ወሰኑ ዓሊ
25 ምንይሉ ወንድሙ