አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – አዳማ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና

የ13ኛው ሳምንት ቀዳሚው ጨዋታ ከመጀመሩ አስቀድሞ እነዚህን መረጃዎች ትጋሩ ዘንድ ጋብዘናል።

በቅዱስ ጊዮርጊስ ሽንፈት ያስተናገዱት አሰልጣኝ አስቻለው ኃይለሚካኤል ትናንት ራሳቸውን ከኃላፊነት እንስተው ዳግም በአመራሮች ጥረት የተመለሱ ሲሆን በቂ የዝግጅት ጊዜ ያልነበራቸው መሆኑ እስካሁንም ተፅዕኖ እንዳሳደረባቸው የተናገሩ ሲሆን ዛሬ በሚጠቀሙት ቡድን ላይ ሦስት የአሰላለፍ ለውጦች አድርገዋል። በለውጦቹ ጉዳት በገጠመው ቴዎድሮስ ገብረእግዚያብሄር ፣ ዳንኤል ተሾመ እና ጀሚል ያዕቆብ ምትክ ሙጃይድ መሀመድ ፣ ታሪክ ጌትነት እና በላይ አባይነህ ጨዋታውን ይጀምራሉ።

ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ነጥብ የተጋሩት አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ዛሬ በስብስባቸው ላይ ሁለት ቅያሪ አድርገው ቀርበዋል። አሰልጣኙ ባለፈው ጨዋታ ተጋጣሚያቸው ክፍተት ሳይሰጣቸው በመቅረቱ ለማስከፈት ያደረጉት ጥረት ያልተሳካ መሆኑን አስበው ዛሬ ተመሳሳይ ፈተና ቢገጥማቸው በተሻለ ሁኔታ ክፍተትን ለማግኘት እንደሚጥሩ ገልፀዋል። ቡድኑ ባደረገው ለውጥ ምንተስኖት ከበደ እና ፍቅረየሱስ ተወልደብርሀን ወደ አሰላለፍ መጥተው ወንድሜነህ ደረጄ እና ዊልያም ሰለሞን አርፈዋል።

ፌደራል ዳኛ ኢሳይያስ ታደሰ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ለመምራት ተመድበዋል።

ቡድኖቹ ለዛሬ ይዘውት የሚገቡት ስብስብ ይህንን ይመስላል ;-

አዳማ ከተማ

23 ታሪክ ጌትነንት
13 ታፈሰ ሰርካ
20 ደስታ ጊቻሞ
44 ትዕግስቱ አበራ
6 እዮብ ማቲያስ
22 ደሳለኝ ደባሽ
14 ሙጃይድ መሀመድ
8 በቃሉ ገነነ
9 በላይ አባይነህ
7 ፍሰሀ ቶማስ
10 አብዲሳ ጀማል

ኢትዮጵያ ቡና

99 አቤል ማሞ
18 ኃይሌ ገብረትንሳይ
22 ምንተስኖት ከበደ
2 አበበ ጥላሁን
11 አሥራት ቱንጆ
15 ሬድዋን ናስር
3 ፍቅረየሱስ ተ/ብርህን
5 ታፈሰ ሰለሞን
17 አቤል ከበደ
10 አቡበከር ናስር
7 ሚኪያስ መኮንን


© ሶከር ኢትዮጵያ