ፋሲል ከነማ ከ ሰበታ ከተማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

09፡00 ሲል በሚጀምረው ጨዋታ ዙሪያ ተከታዮቹን መረጃዎች አሰናድተናል።

አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ሀዋሳ ከተማን ሲያሻንፉ ከተጠቀሙበት ቀዳሚ አሰላለፍ ውስጥ ባደረጉት ብቸኛ ለውጥ የአምስት ቢጫ ካርድ ቅጣት ያለበት አምሳሉ ጥላሁንን በሳሙኤል ዮሃንስ በመለወጥ ለዛሬው ጨዋታ ቀርበዋል።

የሰበታ ከተማው አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ በበኩላቸው ወሳኝ ተጨዋቾቻቸውን ከጉዳት መልስ ያገኙ ዳዊት እስጢፋኖስ ፣ ቡልቻ ሹራ እና ጌቱ ኃይለማርያምን ጉዳት ባስተናገደው ፉዓድ ፈረጃ ፣ ኢብራሂም ከድር እና ዓለማየሁ ሙለታ ቦታ ተክተዋል።

ፌደራል ዳኛ ኡክሊሉ ድጋፌ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ለመምራት ተመድበዋል።

ፋሲል ከነማ

1 ሚኬል ሳማኬ
2 እንየው ካሣሁን
5 ከድር ኩሊባሊ
16 ያሬድ ባየህ
12 ሳሙኤል ዮሐንስ
14 ሀብታሙ ተከስተ
10 ሱራፌል ዳኛቸው
17 በዛብህ መለዮ
7 በረከት ደስታ
19 ሽመክት ጉግሳ
26 ሙጂብ ቃሲም

ሰበታ ከተማ

1 ምንተስኖት አሎ
5 ጌቱ ኃይለማርያም
4 አንተነህ ተስፋዬ
13 መሳይ ጳውሎስ
23 ኃይለሚካኤል አደፍርስ
3 መስዑድ መሀመድ
10 ዳዊት እስጢፋኖስ
15 አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ
17 ታደለ መንገሻ
7 ቡልቻ ሹራ
16 ፍፁም ገብረማርያም


© ሶከር ኢትዮጵያ