ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 15ኛ ሳምንት ቁጥሮች እና መረጃዎች

በአስራ አምስተኛው ሳምንት በተደረጉ ጨዋታዎች ላይ የተመዘገቡ ቁጥራዊ መረጃዎች እና ዕውነታዎችን እንዲህ አቅርበናል።

– በዚህ ሳምንት በተደረጉ ጨዋታዎች 9 ጎሎች ተቆጥረዋል። ይህ ካለፈው ሳምንት በሰባት ጎሎች ያነሰ ነው።

– ሁለት ጎሎች ከእረፍት በፊት ሲቆጠሩ ሰባት ጎሎች ደግሞ ከእረፍት በኋላ ተመዝግበዋል።

– ከዘጠኝ ጎሎች መካከል ምንም የፍፁም ቅጣት ምት ጎል አልተቆጠረም። ይህም በውድድር ዓመቱ ለመጀመርያ ጊዜ ነው።

– ከተቆጠሩት ጎሎች መካከል ሰባት በክፍት ጨዋታ ሲያስቆጥሩ ሁለት (ጋቶች እና አሜ መሐመድ) ከማዕዘን ምት መነሻቸው የሆኑ ጎሎች አስቆጥረዋል።

– የወላይታ ድቻው ጋቶች ፓኖም እና የሀዋሳ ከተማው መስፍን ታፈሰ በግንባር ገጭተው ጎል ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።

– ዘጠኝ ተጫዋቾች ለቡድናቸው ጎል ማስቆጠር ችለዋል። ሁሉም አንድ አንድ ጎል ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።

– አህመድ ሁሴን፣ መስዑድ መሐመድ እና ጋቶች ፓኖም የዓመቱ የመጀመርያ ጎላቸውን በዚህ ሳምንት አስቆጥረዋል።

– 8 ተጫዋቾች ለጎል በማመቻቸት አስተዋፅኦ አድርገዋል።

የዲሲፕሊን ቁጥሮች

– በዚህ ሳምንት 23 የማስጠንቀቂያ ካርዶች ተመዘዋል። ይህም ካለፈው ሳምንት በአስር ቀንሷል።

– ተስፋዬ አለባቸው በሁለተኛ ቢጫ ከሜዳ የወጣ የዚህ ሳምንት ብቸኛ ተጫዋች ነው።

– አይዛክ ኢሲንዴ፣ ተስፋዬ ነጋሽ እና ሀብታሙ ተከስተ በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ቢጫ ካርድ በመመልከት ቀጣይ ጨዋታ የሚያልፋቸው ተጫዋች ሆነዋል።

ዕውነታዎች

– ሙጂብ ቃሲም ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ ጎል ተመልሷል። ቡና ላይ ያስቆጠረው ጎል ወልቂጤ ላይ በዘጠነኛ ሳምንት ካስቆጠረ ከ390 ደቂቃ በኋላ የተገኘ ነው።

– የወልቂጤ ከተማው አጥቂ አህመድ ሁሴን ከድፍን አንድ ዓመት በኋላ ወደ ጎል ተመልሷል። በተሰረዘው የውድድር ዓመት የካቲት ወር ወልዋሎ ላይ የመጨረሻውን ጎል ያስቆጠረው አጥቂ ከአንድ ዓመት ጥበቃ በኋላ ወደ ጎል ተመልሷል።

– ወላይታ ድቻ የቀደመ የመከላከል ጥንካሬው እየተመለሰ ይመስላል። በአራት ተከታታይ ጨዋታዎችም ጎል ሳይቆጥጥበት ወጥቷል።

– ጋቶች ፓኖም ከ32 ወራት በኋላ ለኢትዮጵያ ክለብ ጨዋታ አድርጓል። ቡድኑ ወላይታ ድቻ አዳማን ባሸነፈበት ጨዋታ ለመጀመርያ ጊዜ ለቡድኑ የተሰለፈው ጋቶች ጎል ያስቆጠረ ሲሆን ይሆም ሐምሌ 1 ቀን 2010 መቐለ ኤሌክትሪክ 1-0 ሲያሸንፍ ካስቆጠረው ጎል በኋላ በፕሪምየር ሊጉ ያስቆጠረው የመጀመርያ ጎል ሆኖ ተመዝግቧል።

የሳምንቱ ስታቶች

(ቁጥሮቹ የተገኙት ከሱፐር ስፖርት ነው)

ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ

ከፍተኛ – ወልቂጤ ከተማ (9)
ዝቅተኛ – ኢትዮጵያ ቡና እና አዳማ ከተማ (0)

ጥፋቶች

ከፍተኛ – ሀዲያ ሆሳዕና (18)
ዝቅተኛ – ባህር ዳር ከተማ (10)

ከጨዋታ ውጪ

ከፍተኛ – ጅማ አባ ጅፋር (6)
ዝቅተኛ – ኢትዮጵያ ቡና (1)

የማዕዘን ምት

ከፍተኛ – ቅዱስ ጊዮርጊስ (9)
ዝቅተኛ – ሰበታ እና ሆሳዕና (2)

የኳስ ቁጥጥር ድርሻ

ከፍተኛ – ኢትዮጵያ ቡና (67%)
ዝቅተኛ – ፋሲል ከነማ (33%)


© ሶከር ኢትዮጵያ