ባህር ዳር ከተማ የ2013 የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ቻምፒዮንነቱን አረጋገጠ

የባህር ዳር ከተማ ሴቶች ቡድን አንድ ጨዋታ እየቀረው የሁለተኛ ዲቪዝዮን ቻምፒዮን በመሆን ወደ 2014 የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል።

በሀዋሳ እየተደረገ የሚገኘው እና ሊጠናቀቅ የአንድ ሳምንት ዕድሜ የቀረው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ውድድር ዛሬ ሦስት የ17ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ተደርገዋል። ባህር ዳር ከተማ ጥሩነሽ ዲባባን በቤተልሄም ግዛቸው ብቸኛ ጎል 1-0 በማሸነፍም ነጥቡን 41 አድርሶ ቻምፒዮንነቱን በማረጋገጥ ወደ 2014 የአንደኛ ዲቪዚዮን ውድድር ማደጉን አረጋጥጧል።

የቻምፒዮንነት ዕድል የነበረው ቦሌ ክፍለ ከተማ በንፋስ ስልክ 2ለ1 የተረታ ሲሆን ሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በበኩላቸው ቂርቆስ ክፍለ ከተማን 4ለ0 አሸንፈው ከቦሌ ያላቸውን ልዩነት ወደ አንድ በማጥበብ ወደ አንደኛ ዲቪዝዮን የማደግ ተስፋቸውን አለምልመዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ