ማዳጋስካሮች ልምምዳቸውን አከናውነዋል

ለጨዋታው ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ወደ ባህር ዳር የገቡት ማዳጋስካሮች የመጨረሻ ልምምዳቸውን አመሻሹ ላይ አከናውነዋል።

ባሳለፍነው እሁድ በቻርተር አውሮፕላን ከሃምሳ በላይ አባላት ያሉት የልዑክ ቡድን በመያዝ ባህር ዳር ከተማ የገቡት ማዳጋስካሮች ጃካራንዳ ሆቴል ማረፊያቸው በማድረግ ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሦስት ልምምዳቸውን ሰርተዋል።

የፈረንሳይ ፕሮፌሽናል ሊግ (LFP) ከዚህ ቀደም ባደረጉት ስብሰባ በሊጉ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ከአውሮፓ ኅብረት እና ከአውሮፓ ኢኮኖሚክ ቀጠና ውጪ ወደሚገኝ ሀገር እንዳይወጡ ክልከላ በማስተላለፉ ምክንያት በፈረንሳይ አንደኛ እና ሁለተኛ ዲቪዚዮን የሚጫወቱ ወደ 150 የሚሆኑ የአፍሪካ ሀገራት ዜግነት ያላቸው ተጫዋቾች ለሀገራቸው የሚሰጡት ግልጋሎት አይኖርም ቢባልም የማዳጋስጋር እግርኳስ ፌዴሬሽን ከኤል ኤፍ ፒ ጋር ባደረገው ውይይት የተወሰኑት የቡድኑ አባለት በቻርተር አውሮፕላን በፍጥነት ባህር ዳር ገብተዋል።

ሆኖም የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋች የሆኑት ማርኮ ኢላሂ ማሀትራ እና ራያን ሬቭሎሰንን ጨምሮ አምስት ተጫዋቾች በኮቪድ ምክንያት ከስብስቡ ውጭ ሆነዋል። ለአስራ አምስት ደቂቃ ሜዳ ውስጥ ለዘገባ በቆየንበት አጋጣሚ ታክቲካል ልምምዳቸውን ያልተመለከትን ቢሆንም በዋና አሰልጣኛቸው ኒኮላ ድፕዊ ለቡድኑ አባላትን የመምከር እና ቀለል ያሉ የኳስ ንክኪዎችን ሲያደርጉ ተመልክተናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ