ካሜሩናዊያን ዳኞች የነገውን ጨዋታ ይመሩታል

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ አምስተኛ የምድብ መርሐ ግብር ነገ ኢትዮጵያ ከ ማዳጋስካር የሚያደርጉትን ጨዋታ የካሜሩን ዳኞች ይመሩታል።

ነገ 10:00 ላይ በባህር ዳር ዓለምአቀፍ ስታዲየም የሚደረገውን ይህን ወሳኝ ጨዋታ ካሜሩናዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ዤኖ ፍራን ቢቶ በዋና ዳኝነት ሲመራው፤ የሀገሩ ዜጎች ኤልቪስ ጋይ እና ካሪን አቴዛምቦንግ በረዳት ዳኝነት እንዲሁም ዳግላስ ኮዬቴ በአራተኛ ዳኝነት ተሰይመዋል።

የጨዋታው ኮሚሽነር ዛንዚባራው ምዚ ዛም ሲሆኑ ግብፃዊው አህመድ ዘካርያ የፀጥታ ኃላፊ ሆነው በካፍ ተመድበዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ