አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ሲዳማ ቡና ከ ፋሲል ከነማ

10፡00 ሲል ከሚጀምረው ጨዋታ በፊት እነኚህ መረጃዎችን እንካችሁ ብለናል።

ከደቂቃዎች በፊት ዝናብ ማስተናገድ የጀመረችው ድሬዳዋ አሁንም ድረስ በዝናባማ የአየር ሁኔታ ውስጥ ሆና የጨዋታውን መጀመር እየተጠባባቀች ትገኛለች።

ከደቂቃዎች በኋላ በሚጀምረው ግጥሚያም ሲዳማ ቡና ወልቂጤ ከተማን ሲረታ በተጠቀመበት አሰላለፍ ላይ በመስመር ተከላካይነት ሰንደይ ሙቱኩን ከቅጣት መልስ በአማኑኤል እንዳለ ቦታ የተተቀመ ሲሆን ዮናስ ገረመውም አማካይ ክፍል ላይ ያሬድ ከበደን ተክቶ ጨዋታውን ይጀምራል። 

ሰንደይ እና ዮናስን ጨምሮ 70 80 በመቶው የሚፈልጓቸውን ተጫዋቾች ማግኘታቸውን የገለፁት የሲዳማው አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ አሸንፈው ለመውጣት እንደተዘጋጁ ተናግረዋል።
በፋሲል ከነማ በኩል የተደረገው ብቸኛ ለውጥ ደግሞ ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ በበረከት ደስታ ቦታ ከመስመር የሚነሳ አማካይ በመሆን ጨዋታውን ያከናውናል። 

በባህር ዳሩ ጨዋታ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ያልነበሩት አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ዛሬ ወደ ሜዳ ተመልሰዋል። አሰልጣኙ ስለጨዋታው በሰጡት አስተያየትም የተለየ ዝግጅት ባያደርጉም ከሀዋሳው ውድድር በፊት ድሬዳዋ ላይ ሁሉንም ነጥብ ለመሰብሰብ እና በቶሎ ቻምፒዮንነታቸውን ለማረጋገጥ ቡድናቸው በሙሉ ሀዋስብ ሙሉ ሦስት ነጥብ ለማሳካት እንደሚገባ ተናግረዋል። 

ጨዋታውን ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ በመሀል ዳኝነት ይመሩታል። በረዳት ዳኝነት የትናንት ምሽቱን ጨዋታም የዳኙት ፌደራል ዋና ዳኛ አዳነ ወርቁ እና ረዳት ዳኛ ሶሬሳ ድጉማ ተመድበዋል።

የቡድኖቹ የዛሬ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል:-

ሲዳማ ቡና

23 ፋቢያን ፋርኖሌ
32 ሰንደይ ሙቱኩ
2 ፈቱዲን ጀማል
24 ጊትጋት ኮች
5 መሐሪ መና
16 ብርሀኑ አሻሞ
10 ዳዊት ተፈራ
20 ዮናስ ገረመው
8 ኢኪኪ አፎላቢ
27 ማማዱ ሲዲቤ
9 ሀብታሙ ገዛኸኝ

ፋሲል ከነማ

1 ሚኬል ሳማኬ
2 እንየው ካሣሁን
5 ከድር ኩሊባሊ
16 ያሬድ ባየህ
21 አምሳሉ ጥላሁን
17 ሀብታሙ ተከስተ
10 ሱራፌል ዳኛቸው
17 በዛብህ መለዮ
18 ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ
19 ሽመክት ጉግሳ
26 ሙጂብ ቃሲም


© ሶከር ኢትዮጵያ