አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ባህር ዳር ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና

የ23ኛው ሳምንት የመጨረሻ ቀን ቀዳሚው ጨዋታ ላይ የተደረጉ የአሰላለፍ ለውጦች እና የአሰልጣኞች አስተያየት ይህንን ይመስላል።

ባህር ዳር ከተማዎች ከቅዱስ ጊዮርጊሱ ሽንፉት የሦስት ተጫዋቾች ለውጥ አድርገዋል። መሰመር ተከላካዩ ሚኪያስ ግርማ በሳለአምላክ ተገኘ ሲተካ መሀል ላይ በረከት ጥጋቡ የሳምሶን ጥላሁንን ቦታ ይሸፍናል። ፊት መስመር ላይ ደግሞ ባዬ ገዛኸኝን በመለወጥ ምንይሉ ወንድሙ በአጥቂነት ይጀምራል።

በኢትዮጵያ ቡና በኩል በተደረገው ብቸኛ ለውጥ ደግሞ ሀብታሙ ገዛኸኝ ወደ አሰላለፍ ሲመጣ አቤል ከበደ ከአሰላለፍ ውጪ ሆኗል።

እስከ ሦስት ያለውን ቦታ ይዞ ለመጨረስ የዛሬውን ጨዋታ የግድ ማሸነፍ ይኖርብናል ያሉት አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ተጋጣሚያቸው ጠንካራ መሆኑን አንስተው ሁለቱንም ያማከለ የጨዋታ አቀራረብን ይዘው እንደሚገቡ ጠቁመዋል።

አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ በበኩላቸው ጎል ለማግባት መቸኮል ጎል እንዳናገኙ እንዳደረጋቸው አንስተው በዚህ ረገድ ተጫዋቾቻቸውን እንዳዘጋጁ ገልፀዋል።

ፌደራል ዳኛ ኤፍሬም ደበሌ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት የመምራት ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።

የቡድኖቹ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል :-

ባህር ዳር ከተማ

99 ሀሪስተን ሄሱ
13 አህመድ ረሺድ
15 ሰለሞን ወዴሳ
6 መናፍ ዐወል
18 ሣለአምላክ ተገኘ
12 በረከት ጥጋቡ
21 ፍቅረሚካኤል ዓለሙ
14 ፍፁም ዓለሙ
10 ወሰኑ ዓሊ
7 ግርማ ዲሳሳ
25 ምንይሉ ወንድሙ

ኢትዮጵያ ቡና

99 አቤል ማሞ
11 አሥራት ቱንጆ
4 ወንድሜነህ ደረጄ
22 ምንተስኖት ከበደ
18 ኃይሌ ገብረትንሳይ
8 አማኑኤል ዮሐንስ
5 ታፈሰ ሰለሞን
13 ዊሊያም ሰለሞን
25 ሀብታሙ ታደሰ
10 አቡበከር ናስር
7 ሚኪያስ መኮንን

© ሶከር ኢትዮጵያ