በሴካፋ ዋንጫ የሚወዳደሩ ሀገራት ተለይተው ታውቀዋል

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በባህርዳር ከተማ በሚደረገው የሴካፋ ከ23ዓመት በታች ውድድር ተሳታፊ ሀገራት ተለይተው ታወቁ፡፡

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከሐምሌ 10 ጀምሮ በባህር ዳር ከተማ በሚካሄደው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ አገራት ከ23 ዓመት በታች የእግር ኳስ ውድድር 11 አባል አገራት እና 1 ተጋባዥ አገር ተሳታፊ መሆናቸው የተገለፀ ቢሆንም ሱዳን እና ዲሞክራቲክ ሪፐቡሊክ ኮንጎ ተሳታፊ አለመሆናቸው ታውቋል፡፡

በውድድሩ ሱዳን እንደማትሳተፍ የታወቀ ሲሆን 11 የሴካፋ አባል ሀገራት ውድድሩን የሚሳተፋ መሆናቸውን አወዳዳሪው አካል ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሳውቋል፡፡ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ኤርትራ፣ ቡሩንዲ፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ዛንዚባር፣ ሶማሊያ እና ጅቡቲ በውድድሩ ተሳታፊ መሆናቸው ተረጋግጧል ሲል ፌዴሬሽኑ አሳውቋል፡፡