አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | ኮልፌ ቀራኒዮ ከ ጅማ አባጅፋር

ከደቂቃዎች በኋላ የሚጀምረው የአራተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታን የተመለከቱ መረጃዎች እንዲህ ተዘጋጅተዋል።

በአዳማ ከተማ ከደረሰባቸው ሽንፈት በኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታ ያገገሙት ኮልፌ ቀራኒዮዎች የግብ ዘባቸውን ብቻ በመለወጥ ወደ ሜዳ ገብተዋል። በዚህም ኃይማኖት አዲሱ ከአሰላለፍ ወጥቶ አዲሱ ቦቄ ተሰልፏል። የውድድሩን የመጀመሪያ ሦስት ነጥብ ከሀምበሪቾ ዱራሜ ያገኘው ጅማ አባጅፋርም በተመሳሳይ አንድ ተጫዋች ብቻ ለውጦ ወደ ሜዳ ገብቷል። በዚህም አሠልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ሳዲቅ ሴቾን አሳርፈው ራሂም ኦስማኖን ወደ ሜዳ አስገብተዋል።

ፌዴራል ዳኛ ዳንኤል ግርማይ በሚመሩት ጨዋታ ላይ ቡድኖቹ የሚጠቀሙት ቋሚ አሰላለፍ የሚከተለው ነው።

ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከ

99 አዲስ ቦቄ
21ተመስገን ዘውዱ
3 አቡበከር ከሚል
13 ፉዐድ ነስሩ
11 ኪሩቤል ወንድሙ
5 ፈቱ አብደላ
2 አቡበከር ሸሚል
7 አንዋር ዱላ
8 ደሳለኝ ወርቁ
10 ብሩክ ሙሉጌታ
9 ሀቢብ ከማል

ጅማ አባ ጅፋር

91 አቡበከር ኑሪ
28 ስዩም ተስፋዬ
16 መላኩ ወልዴ 3 አሌክስ አሙዙ
14 ኤልያስ አታሮ
21 ንጋቱ ገብረስላሴ
20 ሀብታሙ ንጉሴ
13 ዋለልኝ ገብሬ
19 ተመስገን ደረሰ
26 ዋውንጎ ፕሪንስ
3 ራሂም ኦስማኖ