የባህር ዳር ስታዲየም የመግቢያ ዋጋ ታውቋል

የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ዋንጫ ቅዳሜ የሚጀመር ሲሆን ሀያ አምስት ሺህ ደጋፊዎች እንዲገቡ የተፈቀደለት የባህር ዳር ስታዲየም የመግቢያ ዋጋም ታውቋል፡፡

በዘጠኝ ሀገራት መካከል በሦስት ምድቦች ተከፍሎ ቅዳሜ ሐምሌ 10 በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች የሚጀምረው የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ሀገራት ዋንጫ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም መከናወን ይጀምራሉ፡፡ ካለ ወንበር ከመቶ ሺህ በላይ ተመልካቾችን በሚይዘው የባህር ዳር ስታዲየም የኮቪድ 19 ህጎችን በጠበቀ መልኩ 25 ሺህ ያህል ደጋፊዎች ገብተው እንዲመለከቱ መወሰኑ የሚታወስ ሲሆን በጨዋታው ለሚታደሙትም የመግቢያ ዋጋም ታውቋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ በዚህ የቁጥር መስፈርት መሠረት ጨዋታዎችን ወደ ስታዲየም ገብቶ መመልከት የፈለጉ ሁሉ በባህር ዳር በሚገኝ ዓባይ ባንክ 100 ብር በአካል አልያም በኢ-ብር አማካኝነት በመክፈል ትኬት በመቁረጥ መመልከት እንደሚችሉ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡