የጣና ሞገዶቹ ተጨማሪ የግብ ዘብ አስፈርመዋል

በዛሬው ዕለት የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር የጨረሱት ባህር ዳር ከተማዎች በሰዓታት ልዩነት ሌላ ግብ ጠባቂ የግላቸው አድርገዋል።

አሠልጣኝ አብርሃም መብራቱን ዋና አሠልጣኝ አድርገው የሾሙት ባህር ዳር ከተማዎች በ2014 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተጠናክሮ ለመቅረብ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ። ክለቡ አመሻሽ ላይ የግብ ዘቡ አቡበከር ኑሪን እና የኤርትራውን አጥቂ ዓሊ ሱሌማንን ዝውውር የጨረሰ ሲሆን አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ውስጥ የሚገኘውን ግብ ጠባቂ ፋሲል ገብረሚካኤልን ማስፈረሙ ታውቋል።

የቀድሞ የፋሲል ከነማ ግብ ጠባቂ ዘንድሮ ወደ ሰበታ ከተማ በማምራት መጫወቱ ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ ከፅዮን መርዕድ እና አቡበከር ኑሪ ጋር ተፎካክሮ ቋሚ ለመሆን የጣና ሞገዶቹን በሁለት ዓመት ውል መቀላቀሉ ታውቋል።