ታታሪው የመስመር ተከላካይ ለሰበታ ከተማ ፊርማውን አኑሯል

በዝውውር ገበያው ላይ በንቃት እየተሳተፉ የሚገኙት ሰበታ ከተማዎች በዛሬው ዕለት የመስመር ተከላካይ ማስፈረማቸው ታውቋል።

አሠልጣኝ ዘላለም ሽፈራውን ዋና አሠልጣኝ አድርገው የሾሙት ሰበታ ከተማዎች ከሰሞኑን በዝውውር ገበያው ላይ የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ። አሁን በተገኘ መረጃ ደግሞ በአዳማ ከተማ የውድድር ዓመቱን ያሳለፈው ታፈሠ ሰርካ ስብስባቸውን መቀላቀሉ ታውቋል።

የቀድሞ የመከላከያ እና መቐለ 70 እንደርታ ተጫዋች የነበረው ታፈሠ አይደክሜ ከሚባሉ የመስመር ተከላካዮች አንዱ እንደሆነ ይታወቃል። አሁን ደግሞ ይህንን ግልጋሎቱን ለሰበታ ከተማ ለመስጠት የሁለት ዓመት ውል ከደቂቃዎች በፊት ፈፅሟል።