ሀዋሳ ከተማ የጋናዊውን ተከላካይ ውል አራዘመ

ጋናዊው የመሐል ተከላካይ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት በሀዋሳ ከተማ ይቆያል ፡፡

ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ውጤታማ ከሆኑ የውጪ ዜግነት ያላቸው ተጫዋቾች መካከል የሚጠቀሰው የመሀል ተከላካዩ ላውረንስ ላርቴ በ2009 ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኃላ ሀዋሳን በመቀላቀል በወጥነት ክለቡን ያለፉትን አምስት ዓመታት እያገለገለ ቀይቷል። ይህ የቀድሞው የአያክስ ኬፕታውን እና ክለብ አፍሪካን ተጫዋች በሀይቆቹ ሰባት ዓመታትን ለመድፈን ውሉን አድሷል፡፡

በንቃት ዝውውሩ ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው ሀዋሳ ከተማ ፀጋሰው ድማሙ፣ በቃሉ ገነነ፣ መሐመድ ሙንታሪ፣ አብዱልባሲጥ ከማል እንዲሁም ኤርሚያስ በላይን ቀደም ብሎ ያስፈረመ ሲሆን የስድስት ተጫዋቾችን ውል ማራዘሙም ይታወሳል፡፡