ወላይታ ድቻ የቀድሞው ግብ ጠባቂውን ዳግም አስፈረመ

የጦና ንቦቹ የቀድሞው ግብ ጠባቂያቸው በሁለት ዓመት ውል አስፈርመዋል፡፡

በዝውውሩ አራት ተጫዋቾችን አስፈርመው የነበሩት ወላይታ ድቻዎች የቀድሞው ግብ ጠባቂያቸው ወንድወሰን አሸናፊን ዳግም አስፈርመዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ሙገር ሲሚንቶን ለቆ በወላይታ ድቻ የተጫወተው እና ከአምስት ዓመት በፊት ክለቡን ከለቀቀ በኃላ በኢትዮጵያ ቡና፣ ስሑል እና ወልዋሎ (ከፈረመ በኋላ ከውድድር ውጪ ሆነዋል) መጫወት የቻለው ወንድወሰን በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት አጋማሹ ላይ ወደ ድሬዳዋ ከተማ አምርቶ በመጫወት አሳልፏል፡፡ በብርቱካናማዎቹ የፍሬው ጌታሁን ተጠባባቂ የነበረው ተጫዋቹ በሁለት አመት ውል በዛሬው ዕለት የቀድሞው ክለቡን በይፋ ተቀላቅሏል፡፡