መስዑድ መሐመድ የቀድሞ ክለቡን ተቀላቀለ

በቅርቡ አሸናፊ በቀለን በዋና አሰልጣኝነት የሾሙት ጅማ አባጅፋሮች የቀድሞ አማካያቸውን ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል

መስዑድ መሀመድ በይፋ ወደ ጅማ አምርቷል፡፡ የቀድሞው የኤሌክትሪክ እና ኢትዮጵያ ቡና የመሐል ሜዳ ኮከብ ቡናማዎቹን ከለቀቀ በኃላ ከዚህ ቀደም በጅማ አባጅፋር የተጫወተ ሲሆን ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት ወደ ሰበታ ከተማ አምርቶ በክለቡ ማሳለፍ ከቻለ በኋላ የሰበታ ከተማ ውሉን አጠናቆ በአንድ ዓመት ውል ጅማን ተቀላቅሏል፡፡