ጅማ አባጅፋር ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን አስፈረመ

ከሰዓታት በፊት መስዑድ መሐመድን የግሉ ያደረገው ጅማ አባ ጅፈር አሁን ደግሞ የመስመር ተከላካይ እና የአማካይ ስፍራ ተጫዋች አስፈርሟል።

ሱሌይማን መሐመድ ከፈራሚዎቹ አንዱ ነው። የቀድሞው የባንኮች እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከላካይ በሱዳን ቆይታ ካደረገ በኋላ በአዳማ ከተማ ለስድስት ዓመታት ሲጫወት የቆየ ሲሆን በዛሬው ዕለት የቀድሞ አሰልጣኙ አሸናፊ በቀለን በመከተል ለጅማ አባጅፋር ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል።

ሦስተኛ ፈራሚ ሆኖ ክለቡን የተቀላለው ወጣቱ አማካይ ሚካኤል ሀሲሳ ሆኗል፡፡ ከሲዳማ ቡና የታዳጊ ቡድን ከተገኘ በኃላ ከ2011 ጀምሮ እስከ ተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ድረስ በዋናው የሲዳማ ቡና ክለብ ውስጥ ግልጋሎት ሲሰጥ የነበረው አማካዩ ወደ ጅማ አባጅፋር አምርቷል፡፡

ጅማ አባጅፋር በቀጣይ ቀናቶችም ተጨማሪ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ድርድር ላይ መሆኑን ሰምተናል።