ሰበታ ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈረመ

ሰበታ ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን በሦስት ዓመት ውል አስፈርሟል።

የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ መሐመድ አበራ የቀድሞ አሰልጣኙን ተከትሎ ወደ ሰበታ ከተማ አምርቷል፡፡ ከሀላባ ከተማ ፕሮጀክት ከተገኘ በኃላ ወደ መከላከያ ተስፋ ቡድን በማምራት መቀላቀል የቻለው ወጣቱ ተጫዋች በ2012 የወቅቱ የመከላከያ አሰልጣኝ የነበሩት አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ወደ ዋናው ቡድን አሳድገውት በክለቡ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴን በማድረግ አስደናቂ አቋሙን ያሳየ ሲሆን እስከ ተጠናቀቀው የውድድር ዓመትም መከላከያ ወደ ከፍተኛ ሊጉ ካሳደጉት ክለቦች መካከል አንዱ ሆኖ በአሳዳጊ ክለቡ ቆይታ ካደረገ በኃላ በዛሬው ዕለት የቀድሞው አሰልጣኙ ዘላለም ሽፈራውን ጥሪ ተቀብሎ በሦስት ዓመት የውል ኮንትራት ሰበታን ተቀላቅሏል፡፡

ተከላካዩ በረከት ሳሙኤል የሰበታ ከተማ ሦስተኛ ፈራሚ ሆኗል፡፡ በድሬዳዋ ከተማ ያለፉትን አምስት ዓመታት በመሐል ተከላካይነት እና በአምበልነት የመራው የቀድሞው የሙገር ሲሚንቶ ተጫዋች ረዘም ያለ ጊዜ የቆየበትን የምስራቁን ክለብ በመልቀቅ አዲሱ የሰበታ ተጫዋች በመሆን በሦስት ዓመት ውል መቀላቀል ችሏል፡፡