በዝውውር መስኮቱ በስፋት ተጫዋች በማስፈረም እና ውል በማራዘም ላይ የሚገኘው ሰበታ ከተማ ማምሻውን የአንድ ተከላካይ ዝውውር አጠናቋል።
በኢትዮ ኤሌትሪክ ከታዳጊነት እድሜው አንስቶ እስከ ዋናው ቡድን ድረስ እድገቱን ጠብቆ እየተጫወተ የሚገኘው ተስፈኛው ተከላካይ ወልደ አማኑኤል ጌቱ ለሰበታ ለሦስት ዓመት ለመጫወት ማምሻውን መፈረሙን አረጋግጧል።
ከኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀርቦለት የነበረው እና በትግራይ ክለቦች ምትክ ወደ ፕሪምየር ሊግ ለመመለስ በነበረው ውድድር ለብሔራዊ ቡድን ለመጫወት የነበረው እድል ያልተሳካለት ወልደ አማኑኤል ለቀጣዩ ዓመት ወደ ፕሪምየር ሊጉ የሚመለሰውን ዝውውር ያደረገ ሲሆን ለሰበታ የኋላ ክፍል አማራጭ እንደሚፈጥር ይጠበቃል።