ወላይታ ድቻ ሰባተኛ ፈራሚውን አግኝቷል

የመስመር አጥቂው ፍሰሀ ቶማስ ወደ ወላይታ ድቻ አምርቷል፡፡

ረፋድ ላይ አዲስ ህንፃን ስድስተኛ ፈራሚ ያደረገው ወላይታ ድቻ የመስመር አጥቂው ፍሰሀ ቶማስን ሰባተኛ ፈራሚ አድርጎ ወደ ክለቡ በሁለት ዓመት ውል አስፈርሟል፡፡ ይህ የቀድሞው የሺንሺቾ የመስመር አጥቂ የ2012 የውድድር ዓመትን ሊጉ በኮቪድ 19 እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ በከፍተኛ ሊጉ ጌዲኦ ዲላ በመጫወት አሳልፎ የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት ወደ አዳማ ከተማ ያመራ ሲሆን ቀሪ የአስራ ስምንት ወራት ውል እያለው ከአዳማ ከተማ በቅርቡ በመቀነሱ ምክንያት በክስ ሂደት ላይ የነበረ ሲሆን የተጫዋቹ እና የክለቡ ጉዳይ ሙሉ ለሙሉ ባይፈታም ወደ ጦና ንቦቹ አምርቷል፡፡