በርካታ ተጫዋቾች ወደ ቡድናቸው እየቀላቀሉ ላይ የሚገኙት ጅማ አባ ጅፋሮች በላይ ዓባይነህን አስፈርመዋል፡፡
በ2007 በቀድሞው አጠራሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሊግ ኮከብ ጎል አግቢ በመሆን ድሬዳዋ ከተማን ወደ ፕሪምየር ሊጉ በማሳደጉ ጉልህ ሚና የነበረው በላይ ድሬዳዋን ከለቀቀ በኋላ በካፋ ቡና፣ ኤሌክትሪክ እና ወልዲያ ከተማ ተጫውቶ አሳልፏል፡፡ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት በአዳማ ከተማ ቆይታ የነበረው አጥቂው በአንድ ዓመት ውል ወደ አባጅፋር ቤት ተጉዟል፡፡