ጅማ አባጅፋር ተጨማሪ ተጫዋች አስፈርሟል

አሠልጣኝ አሸናፊ በቀለን የሾሙት ጅማ አባጅፋሮች ከደቂቃዎች በፊት ተጨማሪ ተጫዋች አስፈርመዋል።

ከቀናት በፊት አሸናፊ በቀለን ዋና አሠልጣኝ አድርገው ከሾሙ በኋላ የተጫዋቾች ዝውውር ገበያ ላይ የተጠመዱት ጅማ አባጅፋሮች በ2013 በወልቂጤ ከተማ ያሳለፈው የተከላካይ አማካይ አልሳሪ አልመሐዲን የግላቸው አድርገዋል።

የቀድሞ የድሬዳዋ ከተማ እና ወልዋሎ ዓ/ዩ ተጫዋች የነበረው አልሳሪ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በወልቂጤ ማሳለፉ ይታወሳል። አሁን ደግሞ በጅማ የእግርኳስ ህይወቱን ለመቀጠል ፊርማውን አኑሯል።