ወጣቱ የመስመር አጥቂ ጅማ አባ ጅፋር አምርቷል

በከፍተኛ ሊግ ጥሩ የውድድር ዓመት ያሳለፈው የመስመር አጥቂ ጅማ አባ ጅፋርን ተቀላቅሏል።

በ2014 የውድድር ዘመን በተሻለ ስብስብ ለመቅረብ በዝውውሩ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው ጅማ አባጅፋር ወጣቱ የመስመር አጥቂ ፍፁም ጥላሁንን በሁለት ዓመት ውል የግሉ አድርጓል።

በኢትዮጵያ ቡና ተስፋ ቡድን ድንቅ እንቅስቃሴ በማሳየት ወደ ዋና ቡድን በማደግ በተወሰኑ ጨዋታዎች ላይ መሳተፍ የቻለው ወጣቱ የመስመር አጥቂ ፍፁም በዘንድሮ የውድድር ዓመት ወደ አዲስ አበባ ከተማ በማምራት የተሳካ ጊዜ ካሳለፈ በኃላ አሁን ማረፊያው ጅማ አባ ጅፋር መሆኑ ተረጋግጧል።