ወደ አንደኛ ሊግ የሚያድጉ ተጨማሪ ቡድኖችን የሚለዩት ጨዋታዎች ረቡዕ ይደረጋሉ

የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና በሀዋሳ ከተማ እየተደረገ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ደርሷል፡፡

ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ስምንት ክለቦች ወደ አንደኛ ሊጉ መግባታቸውን ያረጋገጡ ሲሆን ተሸናፊዎቹ እርስ በእርስ ተጫውተው አራት ክለቦች የሚለዩበት መርሐግብር ረቡዕ ነሐሴ 5 በደቡብ ኢትዮጵያ ኮሌጅ ሜዳ ጨዋታቸው ይከውናል፡፡ ይህን ጨዋታ የሚያሸንፉ አራት ክለቦች ስምንቱን ቀድመው ማለፋቸውን ያረጋገጡ ክለቦችን ተከትለው ማደጋቸውን ይወስናሉ፡፡

ወደ አንደኛ ሊግ ለማለፍ የሚደረጉ ጨዋታዎች

ምኅረት ከ ሊሙገነት 2፡00
አዲስ ቅዳም ከ ካራማራ ክለብ 4፡00
ቦዲቲ ከተማ ከ ወንዶ ገነት 7፡00
ቡሬ ዳሞት ከ ኑዌር ዞን 9፡00

በተመሳሳይ ረቡዕ በሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ አስቀድመው ወደ አንደኛ ሊጉ ያደጉት ስምንት ክለቦች ወደ ግማሽ ፍፃሜ ለመሸጋገር ይፋለማሉ፡፡

ቦሌ ክፍለከተማ ከ ዱራሜ ከተማ 2፡00
ካማሺ ከተማ ከ ምስራቅ ክፍለከተማ 4፡00
ቡሳ ከተማ ከ ቫርኔሎ ወረዳ 13 7፡00
ዱከም ከተማ ከ ጋምቤላ አብይ አካዳሚ 9፡00