ወደ ሴቶች ሁለተኛ ዲቪዚዮን ያደጉ ክለቦች ሙሉ በሙሉ ተለይተው ታውቀዋል

በሁለት ምድብ ተከፍሎ በአስር ክለቦች መካከል በሀዋሳ ሲደረግ የነበረው የክልል ክለቦች ሻምፒዮና የምድብ ጨዋታዎች ተጠናቀዋል፡፡

ወደ ኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዲቪዚዮን የሚያድጉ ክለቦችን ለመለየት ለመጀመሪያ ጊዜ እየተደረገ ያለው ይህ ውድድር ከቀናቶች በፊት አላፊ ስድስት ቡድኖች ተለይተው የታወቁ ሲሆን የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ትላንት በሀዋሳ ግብርና ኮሌጅ ተከናውነው ቀሪዎቹ ሁለት ቡድኖቹም ታውቀዋል፡፡

ወላይታ ዞን 3-0 ሰበታ ከተማ
ሱሉልታ ከተማ 1-2 ፔንዳ ክለብ
ሀላባ ዞን 10-1 ምስራቅ ክፍለከተማ
አለታ ወንዶ 0-3 አሰላ ከተማ

በተጠቀሱት ጨዋታዎች እና ቀደም ብለው በተመዘገቡ ውጤቶች መሠረት ከምድብ ሀ አራዳ ክፍለከተማ፣ ሀላባ ዞን፣ ወላይታ ዞን እና ሰበታ ከተማ፤ ከምድብ ለ ሱሉልታ ከተማ፣ ከንባታ ዞን፣ አሰላ ከተማ እና ፔንዳ ክለብ ማለፋቸውን ሲያረጋግጡ ከሲዳማ ክልል የተወዳደሩት ምስራቅ ክፍለከተማ እና አለታ ቤዛ ውሀ ወደ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ሳይገቡ ከምድባቸው ወድቀዋል፡፡

የፊታችን ማክሰኞ ነሐሴ 5 የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

ሱሉልታ ከተማ ከ ሀላባ ዞን 8፡00
አራዳ ክፍለከተማ ከ ከምባታ ዞን 10፡00