ብርቱካናማዎቹ የመስመር ተከላካያቸውን ውል አድሰዋል

በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት ወደ ድሬዳዋ አምርቶ የነበረው የመስመር ተከላካይ ለተጨማሪ ዓመት በክለቡ ለመቆየት ፊርማውን አኑሯል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት አጋማሽ ላይ ወደ ድሬዳዋ ከተማ አቅንቶ በቋሚነት ክለቡን ሲያገለግል የነበረው የመስመር ተከላካዩ ዐወት ገብረሚካኤል ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ከሰሞኑን ከክለቡ ጋር ለመቀጠል ድርድር ሲያደርግ ነበር። ይህ ድርድር ፍሬ አግርቶም ተጫዋቹ ዳግም በቡርትካናማዎቹ መለያ ለመዝለቅ ፊርማውን በዛሬው ዕለት ማኖሩን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

ከመብራት ኃይል ታዳጊ ቡድን የተገኘው የቀኝ መስመር ተከላካዩ ዐወት አሳዳጊ ክለቡን ካገለገለ በኋላ ወደ ጅማ አባጅፋር እና ስሑል ሽረ አምርቶ መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን በቀጣይ ሁለት ዓመታትም በድሬዳዋ የእግርኳስ ህይወቱን የሚቀጥል ይሆናል።