ሲዳማ ቡና ከግብ ጠባቂው ጋር በስምምነት ተለያየ

ሲዳማ ቡናን ያለፉትን አምስት ዓመታት ያገለገለው ግብ ጠባቂ በስምምነት ተለያይቷል፡፡

በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ እየቀላቀለ የከረመው እና የሦስት ነባሮችን ውልም ያደሰው ሲዳማ ቡና ከመሳይ አያኖ ጋር ከአምስት ዓመታት በኋላ በዛሬው ዕለት በስምምነት በይፋ መለያየቱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች፡፡የቀድሞው የደቡብ ፖሊስ እና አርባምንጭ ከተማ ግብ ጠባቂ 2009 መስከረም ወር ላይ ሲዳማ ቡናን የተቀላቀለ ሲሆን ክለቡንም በቋሚ ተሰላፊነት እና አንዳንድ ጊዜም በአምበልነት ላለፉት አምስት ዓመታት ቆይታን አድርጓል፡፡ ግብ ጠባቂው በሲዳማ ቡና የሚያቆየው የአንድ ዓመት ቀሪ ውል የነበረው ቢሆንም ያስገባው የልቀቁኝ ጥያቄ ተቀባይነት በማግኘቱ በዛሬው ዕለት በስምምነት ተለያይቷል፡፡

ከረጅም ዓመታት በኃላ ከክለቡ ጋር መለያየቱ ዕውን የሆነው ግብ ጠባቂው ከሦስት የተለያዩ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች ጋር ስሙ እየተያያዘ ሲሆን በቅርቡም ቀጣይ ማረፊያው የሚታወቅ ይሆናል፡፡