የወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ የቻምፒየንስ ሊግ ተጋጣሚውን አውቋል

በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ኢትዮጵያን የሚወክለው ፋሲል ከነማ ተጋጣሚውን አውቋል።

ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የሚወክለው ፋሲል ከነማ በመጀመሪያ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የሱዳኑን ክለብ አል ሂላል እንደሚገጥም ከደቂቃዎች በፊት የወጣው ድልድል አስታውቋል። ፋሲል የመጀመሪያ ጨዋታውን በሜዳው ሲያደርግ ከሳምንት በኋላ ደግሞ የመልሱን ጨዋታ ወደ ሱዳን ተጉዞ የሚከውን ይሆናል።

ከትናንት በስትያ ልምምዳቸውን በባህር ዳር የጀመሩት ፋሲል ከነማዎች የመጀመሪያ ዙሩን ጨዋታ የሚያሸንፉ ከሆነ ከያንግ አፍሪካ እና ሪቨርስ ዩናይትድ አሸናፊ ጋር በሁለተኛ ዙር የቅድመ ማጣሪያ የሚጫወቱ ይሆናል።