ዋልያዎቹ ጋና እና ዚምባብዌን የሚገጥሙባቸው ቀናት ታውቀዋል

ለካታሩ የ2022 ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመርያ ሁለት ጨዋታዎቿን በዓመቱ መጨረሻ የምታከናውነው ኢትዮጵያ ጨዋታ የምታደርግባቸው ቀናትን አውቃለች።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው በምድብ 7 ከጋና፣ ዚምባብዌ እና ደቡብ አፍሪካ ጋር የተደለደለችው ኢትዮጵያ የመጀመርያ ጨዋታዋን ነሐሴ 28 ወደ ጋና አምርታ የምታከናውን ሲሆን ቀጣዩን ጨዋታ ጳጉሜ 2 ላይ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ዚምባብዌን ታስተናግዳለች።

ብሔራዊ ቡድኑ በአዳማ በመክተም ለጨዋታዎቹ ዝግጅቱን ማድረግ ከጀመረ ከሳምንት በላይ እንዳስቆጠረ ይታወቃል።