ድሬዳዋ ከተማ አማካይ ለማስፈረም ተስማማ

የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ብርቱካናማዎቹን ለመቀላቀል ተስማምቷል፡፡

የ2014 የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ እየተመሩ በሀዋሳ ከተማ ታደሰ እንጆሪ ሆቴል በማረፍ የጀመሩት ድሬዳዋ ከተማዎች የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነው ብሩክ ቃልቦሬን በስብሰባቸው ውስጥ በማካተት መሥራት መጀመራቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡

የቀድሞው የወላይታ ድቻ፣ ወልድያ ፣ አዳማ ከተማ እና እንዲሁም የተጠናቀቀውን የውድድር አመት ከሀድያ ሆሳዕና ጋር በውዝግብ ከተለያዩ ተጫዋቾች መሀል አንዱ እስኪሆን ድረስ የቡድኑ አባል የነበረው ተጫዋቹ አሁን ደግሞ ለቀጣዩ የውድድር ዓመት በድሬዳዋ ከተማ መለያ ለመታየት ከስምምነት ደርሷል፡፡