አባ ጅፋሮች አዲስ ምክትል አልጣኝ ቀጥረዋል

በቢሸፍቱ ከተማ ቅድመ ዝግጅታቸውን እያደረጉ የሚገኙት ጅማ አባጅፋሮች አዲስ ምክትል አሰልጣኝ ማግኘታቸው ታውቋል።

በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ እየተመሩ ወጣት እና ልምድ ያላቸውን ተጫዋቾች ወደ ስብስባቸው በመቀላቀል ዝግጅታቸውን ከሳምንት በፊት የጀመሩት ጅማ አባጅፋሮች ሁለተኛ ምክትል አሰልጣኝ ሾመዋል። ሁለተኛ ምክትል በመሆን ቡድኑን የተቀላቀሉት ቀድሞ ከአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ጋር በሀድያ ሆሳዕና አብረዋቸው የሰሩት ዶ/ር ኢያሱ መርሐፅድቅ ናቸው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ  ዶ/ር ኢያሱ አሁንም አሰልጣኝ አሸናፊን በመከተል የጅማ አባጅፋር ሁለተኛ ምክትል አሰልጣኝ መሆናቸው ተረጋግጧል። አሰልጣኝ ኢያሱ በቢሸፍቱ ከተማ በመገኘት የቡድኑ የዝግጅት አካል በመሆን እያሠሩ መሆናቸውንም ሰምተናል።
በሌላ ዜና ጅማ አባ ጅፋፋሮች በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ ተጨማሪ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው እንደሚቀላቅሉ የክለቡ አመራሮች ገልፀውልናል።