ድሬዳዋ ከተማ የአጥቂውን ውል አራዝሟል

በብርቱካናማዎቹ መለያ ጥሩ ዓመት ያሳለፈው አጥቂ ለተጨማሪ ዓመት በክለቡ ውሉን አራዝሟል፡፡

በሀዋሳ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ አማካኝነት እየከወነ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ ቀሪ አንድ ዓመት በክለቡ የነበረው አጥቂው ሙኽዲን ሙሳን ተጨማሪ ዓመት ለማቆየት ውሉን አራዝሞለታል፡፡

የቀድሞው የናሽናል ሲሚንት እና ሀዲያ ሆሳዕና ተጫዋች ከ2010 ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ እየተጫወተሚገኝ ሲሆን ባለፈው ዓመት የሁለት ዓመት ኮንትራት መፈራረሙ የሚታወስ ነው። በዚህም የአንድ ዓመት ውል ቢቀረውም ተጨማሪ አንድ ዓመት በመጨመር እስከ 2015 በድሬዳዋ እንደሚቆይ ክለቡ ገልጿል።