ሀድያ ሆሳዕና ግብ ጠባቂ አስፈረመ


ከሳምንታት በፊት ከሲዳማ ቡና ጋር በስምምነት የተለያየው ግብ ጠባቂ በአንድ ወደ ሀድያ ሆሳዕና አቅንቷል፡፡

ከሀያ ቀናት በፊት ከወላይታ ድቻ ወደ ሀድያ ሆሳዕና አምርቶ የነበረው ግብ ጠባቂው መክብብ ደገፉ ከክለቡ ጋር በስምምነት ከተለያየ ከአንድ ቀን በኋላ በምትኩ መሳይ አያኖ በይፋ በዛሬው ዕለት በአንድ ዓመት ውል ሀድያ ሆሳዕናን ተቀላቅሏል፡፡ የቀድሞው የደቡብ ፓሊስ እና አርባምንጭ ከተማ ግብ ጠባቂ የሆነው መሳይ አያኖ በሲዳማ ቡናን ከ2009 ጀምሮ ጥሩ ጊዜ በክለቡ ማሳለፉ የሚታወስ ሲሆን ባለፈው ክረምት ወደ ሆሳዕና ለማምራት ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም ኋላ ላይ በሲዳማ ቡና ውሉን ማራዘሙ የሚታወስ ነው።፡፡

ግብ ጠባቂው በቀጣዩ የውድድር ዓመት በሲዳማ ቡና የሚያቆየው ቀሪ ውል እያለው በስምምነት መለያየቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ በአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ለሚመራው ሀድያ ሆሳዕና ለአንድ ዓመት ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል፡፡