የነገውን ጨዋታ የሚመሩት ዳኞች ታውቀዋል

ነገ በባህር ዳር ዓለምአቀፍ ስታድየም የሚደረገውን ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ባህር ዳር ደርሰዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ2022 በኳታር አስተናጋጅነት ለሚደረገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታውን በማድረግ ላይ ይገኛል። የማጣሪያው አካል የሆነውን የምድቡን ሁለተኛ ጨዋታም ነገ ባህርዳር ላይ የዚምባብዌ አቻውን በመግጠም እንደሚከውን ይጠበቃል። ይህንን ተጠባቂ ጨዋታም ለመዳኘት የተመደቡት ዳኞች ታውቀዋል።

በመሀል እና በረዳት ዳኝነት የተመደቡት አርቢትሮች የሲሽየልስ ዜጎች ሲሆኑ የመሀል ዳኛው በርናንድ ካሚሊ ሲባሉ ረዳቶቻቸው ደግሞ ሀንስለይ ዳኒ ፔትሩሲ እና ስቲቭ ጆናታን ማሪይ ይሰኛሉ። አራተኛው ዳኛ ከኮትዲቯር የሆኑት ሶንጊፎሉ ይዮ እንዲሁም ኮሚሽነሩ ኤርትትራዊው ቹቹ ጉሽ ገብረመድህን መሆናቸውም ታውቋል።