ጅማ አባ ጅፋር ከሁለት ተጫዋቾች ጋር ተለያይቷል

ባሳለፍነው የውድድር ዘመን ጅማ አባ ጅፋርን የተጫወቱት ሁለት አማካዮች ክለቡ ጋር መለያየታቸው ተሰምቷል።

በ2013 በአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማርያም ይመራ በነበረው የጅማ አባ ጅፋር ስብስብ ውስጥ በውድድሩ አጋማሽ ላይ የተቀላቀሉት አማኑኤል ተሾመ እና ዋለልኝ ገብሬ ከጅማ አባጅፋሮች ጋር መለያየታቸው ታውቋል። ቀሪ የስድስት ወር ኮንትራት ያላቸው ሁለቱ አማካይ ከቡድኑ ጋር ቢሸፍቱ በመግባት ሲዘጋጁ የቆዩ ቢሆንም ከክለቡ ጋር በስምምነት መለያየታቸው ታውቋል።

ጅማ አባ ጅፋር የትግራይ ቡድኖችን ለመተካት በተደረገው የሀዋሳው ውድድር ከወረደበት ሊግ ዳግም እንዲመለስ አስተዋፅኦ ያደረጉት ሁለቱ ተጫዋቾች ቀጣይ ማረፍያ በቅርቡ ይታወቃል።