ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ድሬዳዋ ከተማ ወጣት ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል

ቀደም ብሎ በርካታ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሎ የነበረው ድሬዳዋ ከተማ ሴቶች ቡድን ሁለት ወጣት ተጫዋቾችን አስፈርሟል።

በአሰልጣኝ ብዙአየው ጀምበሩ የሚመሩት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ተወዳዳሪው ድሬዳዋ ከተማ ለ2014 የውድድር ዘመን በቅርቡ ወደ ዝግጅት የሚገባ ሲሆን አሁንም ቡድኑን ለማጠናከር ሶስት ወጣት ተጫዋቾች በድሬዳዋ ውስጥ ከሚገኙ ቡድኖች ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡

በአማካይ ስፍራ የሚጫወቱት ጥሩዬ ምስጋናው ፣ እድላዊት ለማ እና ሀና ሰጥዬ ክለቡን የተቀላቀሉ አዳዲስ ወጣት ተጫዋቾች ናቸው፡፡