የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሰዓት ማሻሻያ ተደርጎበታል

ነገ የሚጀምረው የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የጨዋታ ሰዓቶች ላይ ሽግሽግ ተደርጓል።

በአስራ ስድስት ክለቦች መካከል የሚደረገው የዘንድሮ የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ከነገ አንስቶ በሀዋሳ ከተማ መደረግ ይጀምራል። የውድድሩ የበላይ አካል የሆነው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበርም የጨዋታ ሰዓቶቹ 9 እና 1 ሰዓት እንደሆነ ቢገልፅም ዛሬ በተገኘ መረጃ የመጀመሪያ የሦስት ሳምንት ጨዋታዎች ላይ የሰዓት ለውጥ እንደተደረገ አውቀናል።

በዚህም ከነገ ጀምሮ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም የሚደረጉት ጨዋታዎች 8 እና 12 ሰዓት እንደሆነ አረጋግጠናል። ይህንን ተከትሎም ነገ 8 ሰዓት ሀዋሳ ከተማ ከጅማ አባጅፋር ሲጫወቱ 12 ሰዓት ደግሞ ድሬዳዋ ከተማ ከወላይታ ድቻ የሚጫወቱ ይሆናል። ሁለቱም ጨዋታዎች በዲ ኤስ ቲቪ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን እንደሚኖራቸውም ሰምተናል።