አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | ጅማ አባጅፋር ከአዳማ ከተማ

የዕለቱን የመጀመሪያ ጨዋታ የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎች እንደሚከተለው አሠናድተናል።

በመጀመሪያው የሊጉ መርሐ-ግብር በሀዋሳ ከተማ አንድ ለምንም የተረታው ጅማ አባጅፋር ሦስት ነጥብ ካስረከበበት ጨዋታ 4 ለውጦችን አድርጎ ወደ ሜዳ ይገባል። በዚህም የ7 ጨዋታ ቅጣት የተላለፈበት ዳዊት እስቲፋኖስን በመስዑድ መሐመድ፣ የግብ ዘቡ ዮሐንስ በዛብህን በታምራት ዳኜ፣ አስናቀ ሞገስ በዱላ ሙላቱ እንዲሁም ሽመልስ ተገኝን በሱራፌል አወል ለውጠው ወደ ሜዳ ገብተዋል። የቡድኑ አሠልጣኝ አሸናፊ በቀለም ከጨዋታው መጀመር በፊት የመጀመሪያ ጨዋታቸውን መሸነፋቸውን አስታውሰው በቀጣይ መሸነፍ ከባድ ስለሆነ ለማሸነፍ ጠንክረው ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ተናግረዋል።

ተጋባዦቹ አዳማ ከተማዎች ደግሞ ነጥብ ከተጋሩበት የወልቂጤ ግጥሚያ ሦስት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም ምንተስኖት አዳና፣ ዮናስ ገረመው እና አቡበከር ወንድሙ አርፈው ዮሴፍ ዮሐንስ፣ ኤሊያስ ማሞ እና አብዲሳ ጀማል የመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ ተካተዋል።

አሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ደግሞ በቅድመ ጨዋታ አስተያየታቸው ዓመቱ መጀመሪያ ላይ እንደመሆናቸው ማሸነፍ እንደሚፈልጉ ነገርግን ከጅማ ከባድ ፈተና እንደሚጠብቃቸው ጠቅሰዋል።

ከደቂቃዎች በኋላ የሚጀምረውን ፍልሚያ ፌዴራል ዋና ዳኛ ዳንኤል ግርማይ የሚመሩት ይሆናል።

የሁለቱ ቡድኖች አሠላለፍም የሚከተለው ነው።

ጅማ አባጅፋር

90 ታምራት ዳኜ
20 በላይ አባይነህ
18 ያብስራ ሙሉጌታ
9 ዱላ ሙላቱ
4 አሳህሪ አልማዲ
15 ተስፋዬ መላኩ
8 ሱራፌል አወል
24 መሐመድ ኑርናስር
3 መስዑድ መሐመድ
7 እዮብ አለማየሁ
17 ዳዊት ፍቃዱ

አዳማ

1 ሴኩምባ ካማራ
4 ሚሊዮን ሠለሞን
13 አሚን ነስሩ
80 ቶማስ ስምረቱ
7 ደስታ ዮሐንስ
6 ዮሴፍ ዮሐንስ
14 ኤሊያስ ማሞ
8 አማኑኤል ጎበና
10 አብዲሳ ጀማል
9 አሜ መሐመድ
12 ዳዋ ሁቴሳ