የአሰልጣኞች አስተያየት | ቅዱስ ጊዮርጊስ 4-1 ኢትዮጵያ ቡና

በቅዱስ ጊዮርጊስ አሸናፊነት ከተጠናቀቀው የሸገር ደርቢ በኋላ የቡድኖቹ አሰልጣኞች ለሱፐር ስፖርት ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

ምክትል አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

ስለጨዋታው

ተጫዋቾቼ በጣም ጥሩ ነገር ነው ያደርጉት። ማድረግ ያለባቸው እና የተነጋገርነውን ነገር ስላረጉልኝ በጣም ረክቼባቸዋለሁ።

ስለመጀመሪያው አነጋጋሪ ጎል

እኔ ሙሉ ለሙሉ ስላላየሁት ይሄ ነው ብዬ መፍረድ ስለማልችል መናገር አልችልም ስለእሱ ኳስ።

ስለቡድኑ ጠንካራ ጎን

ኢትዮጵያ ቡናዎች ኳሶቻቸውን ሜዳቸው ላይ ለማንሸራሸር ስለሚፈልጉ እኛ የመከላከል ወረዳችንን አደራጅተን ከእነሱ ስህተቶች ካገኘነው ኳስ ለማጥቃት የተነጋገርነውን አስተካክለው ስላደረጉ በጣም ደስ ብሎኛል። ከእነሱ ስህተቶች ነው ኳሶቻቸውን የምናገኘው ፤ የሰራነውን ሥራ ነው ያገኘነው።

የጨዋታው ወሳኝ ስለነበረው ጎል

ሁለት ለዜሮ እየመራን ነበር። ሌላ ነገር መናገር አልፈልግም ሦስተኛውን ጎል ስንገባ ማረጋገጣችንን አወቅን። አራተኛውም ለእኔ ሁሉም ጎሎች ማረጋገጫ ጎሎች ናቸው ለቅዱስ ጊዮርጊስ። በዚሁ አጋጣሚ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎችን ከአዲስ አበባ ድረስ መጥተው ይህን ጨዋታ ለማየት ስለመጡ እንኳን ደስ ያላችሁ እላችኋለው።

ስለቸርነት ጉግሳ የግራ መስመር ተከላካይነት

እኛ የምንፈልገው ሌላ የራሳችን ታስክ አለ። በዛ ታስክ ውስጥ ነው እሱን እዛ ቦታ ላይ የምናጫወተው እንጂ ላይቀጥልም ይችላል። ግን የኛ የራሳችን የምናስበው እና የምንፈልገው ነገር ስለነበር ነው በዛ ቦታ ላይ ያጫወትነው።

አሰልጣኝ ካሣዬ አራጌ – ኢትዮጵያ ቡና

ስለጨዋታው

አጠቃላይ የነበረው ነገር ጥሩ ነው። አላውቅም እንግዲህ ምን ያህል ስሜት እንደሚሰጥ ፤ አስቸጋሪ ነው። ጨዋታው ጥሩ ነው ማለት ጨዋታ ለሚገባው ሰው ነው። ጥሩ ነበር በአጠቃላይ።

ስለመጀመሪያው ጎል

ጎሉን ያስቆጠረው ተጫዋች ነገሩን ሳያስተውለው ከሆነ ምንም ማድረግ አትችልም። ሆነ ብለው ያደረጉት ከሆነ ግን ለጊዮርጊስ አሳፋሪ ታሪክ ነው። እኔ ይሄንን ነው የምለው።

ሁለት ተከላካይ አማካዮች ስለመጠቀማቸው

እንደዛ አልነበረም የምንጫወተው። 1-4-3-3 ነው የምንጫወተው አማኑኤል እና ሮቤል ይቀያየሩ ነበር እዛ ቦታ ላይ። እንጂ በሁለት ተከላካይ አማካይ አልነበረም ፎትሜሽኑ። ምክንያቱም ከሲዳማ ጋር ስንጫዉት ከዕረፍት በኋላ ያንን ተጠቅመን ነበር። ከጀርባ ሆነው የሲዳማ ተጫዋቾች የሚቀበሉ ተጫዋቾች ስለነበሩ እሱን ለመቆጣጠር የራሱ አሉታዊ ጎን ነበረው። ስለዚህ በዛ መቀተል አልፈለግንም። በዛ መልኩ አልነበረም የተጫወትነው።

ረጃጅም ኳሶችን ስለመጠቀማቸው

መጀመሪያ አካባቢ እነሱ ጋር የነበረውን ግምት ለማጥፋት የተወሰኑ ኳሶች እንደዛ ተጠቅመናል። ከዛ በኋላ ግን ክፍተቶች ማግኘት ጀምረን ነበር ፤ በእነዛ ክፍተቶች እየተጫወቱ የእኛ ልጆች መውጣት ጀምረው ነበር።

ውጤቱ በውድድር ዓመቱ ላይ ስላለው ተፅዕኖ

ከውጤት አንፃር ስታየው የተፈጠረ ክፍተት አለ። ግን የምንፈልገውን ነገር ከመጠበቅ አንፃር የልጆቹን አዕምሮ መጠበቅ ከተቻለ ጥሩ ነው ያለው ነገር። ብዙ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር የለም። ግን ያ ነገር በውጤትም መታጀብ እንዳለበት ይገባኛል።