አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | ድሬዳዋ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

የሦስተኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን የመጀመሪያ ጨዋታን የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎች እንደሚከተለው ተሰናስለዋል።

ዓመቱን በድል ጀምረው በሁለተኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታ በሲዳማ ቡና የተረቱት ድሬዳዋዎች ሦስት ነጥብ ካስረከቡበት ፍልሚያ ሦስት ለውጦችን አድርገው ወደ ሜዳ ገብተዋል። በዚህም ሚኪያስ ካሣሁንን በመሐመድ አብዱለጢፍ፣ አብዱርሀማን ሙባረክን በማማዱ ሲዲቤ እንዲሁም አቤል ከበደን በአውዱ ናፊዩ ለውጠዋል።

ተጠባቂውን የሸገር ደርቢ በበላይነት ያጠናቀቁት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ደግሞ ሁለት ለውጦችን ብቻ አድርገዋል። በለውጦቹም ከነዓን ማርክነህ እና ግብ ጠባቂው ባህሩ ነጋሽ በደስታ ደሙ እና ቻርለስ ሉክዋጎ ተተክተዋል።

ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት የድሬዳዋው አሠልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ተጋጣሚያቸው አሸንፎ መምጣቱን እነሱ ደግሞ ተሸንፈው መቅረባቸውን አስታውሰው ከኳስ ጋር ዘለግ ያለውን ጊዜ በማሳለፍ አጥቅተው እንደሚጫወቱ ተናግረዋል። በተቃራኒው የዋና አሠልጣኙ ዝላትኮ ክራምፖቲችን አለመኖር ተከትሎ ቡድኑን የሚመሩት ምክትል አሠልጣኙ ዘሪሁን ሸንገታ ደግሞ የደርቢው ድል ውጤት ትልቅ ስንቅ እንደሆነ ተናግረው የዛሬው ጨዋታ አዲስ በመሆኑ እንደ አዲስ እንደተዘጋጁ አመላክተዋል።

ይህንን ጨዋታ ፌዴራል ዳኛ ሚካኤል ጣዕመ በመሐል ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል።

ቡድኖቹ ወደ ሜዳ የሚያስገቡት የመጀመሪያ አሰላለፍም የሚከተለው ሆኗል።

ድሬዳዋ ከተማ

30 ፍሬው ጌታሁን
2 እንየው ካሳሁን
13 መሳይ ጳውሎስ
20 መሐመድ አብዱለጢፍ
4 ሄኖክ ኢሳይያስ
16 ብሩክ ቃልቦሬ
5 ዳንኤል ደምሴ
19 ሙኸዲን ሙሳ
15 አውዱ ናፊዩ
9 ጋዲሳ መብራቴ
25 ማማዱ ሲዲቤ

ቅዱስ ጊዮርጊስ

30 ቻርለስ ሉክዋጎ
14 ሄኖክ አዱኛ
4 ምኞት ደበበ
24 ፍሪምፖንግ ሜንሱ
12 ቸርነት ጉግሳ
20 በረከት ወልዴ
5 ሀይደር ሸረፋ
6 ደስታ ደሙ
7 ቡልቻ ሹራ
10 አቤል ያለው
28 ኢስማኤል ኦሮ-አጎሮ