በ19ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በተካሄዱ ሶስት ጨዋታዎች መሪዎቹ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሲዳማ ቡና ሲያሸንፉ በወራጅ ቀጠና የሚገኙት ሙገር እና ዳሽን አቻ ተለያይተዋል፡፡
ይርጋለም ላይ ደደቢትን ያስተናገደው ሲዳማ ቡና 2-0 በማሸነፍ ካለፈው ሳምንት ሽንፈቱ አገግሟል፡፡ የሲዳማ ቡናን ሁለት ግቦች ከመረብ ያሳረፈው በጥሩ አቋም ላይ የሚገኘው ኬንያዊው ኤሪክ ሙራንዳ ው፡፡ ሲዳማ ድሉን ተከትሎ ነጥቡን 38 በማድረስ ከቅዱ ጊዮርጊስ በግብ ልዩነት ተበልጦ 2ኛ ደረጃን ይዟል፡፡
አሰላ ላይ ዳሽን ቢራን ያስተናገደው ሙገር ሲሚንቶ ካለ ግብ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡ የአቻ ውጤቱን ተከትሎ ሁለቱም ቡድኖች ደረጃቸውን ለማሻሻል የነበራቸውን እድል አባክነዋል፡፡
በሸገር ደርቢ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ቡናን 2-0 በማሸነፍ መሪነቱን በግብ ክፍያ መምራቱን ቀጥሏል፡፡ የጊዮርጊስን የድል ግቦች ከመረብ ያሳረፉት ብሪያን ኡሞኒ እና በኃይሉ አሰፋ ናቸው፡፡