ናይጄርያዊው አጥቂ ሳሙኤል ሳኑሚ ዘንድሮ ከደደቢት ጋር መልካም የውድድር ዘመን እያሳለፈ ይገኛል፡፡ በዛሬው ጨዋታ ሁለት ግቦች አስቆጥሮም በ12 ግብ የከፍተኛ ግብ አግቢነቱን ፉክክር ተቀላቅሏል፡፡ አጥቂው ከዛሬው ጨዋታ በኋላ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አጭር ቆይታ አድርጎ ነበር፡፡
ስለ ዛሬው ድል
ጨዋታው ጥሩ ነበር፡፡ ከጨዋታው በፊት አስበነው የገባነውን አሳክተን ድል አድርገን ወጥተናል፡፡፡፡
ስለ ኮከብ ግብ አስቆጣሪነት ክብር
በርካታ ተጫዋቾች ለከፍተኛ ግብ አግቢነቱ እየተፎካከሩ ነው፡፡ እኔም ይህንን ክብር ለማሳካት እስከ መጨረሻው እተጋለሁ፡፡
ስለ ዮሃንስ ሳህሌ
ጥሩ አሰልጣኝ ነው፡፡ የሚያሰለጥንበት መንገድ ተስማምቶናል፡፡ ቡድኑን ወደ ጥሩ መንገድ እየመራው ነው፡፡
ስለ አጥቂ ጥምረት
ከምርጥ አጥቂዎች ጋር እየተጫወትኩ ነው፡፡ ከጨዋታ በፊት እንነጋገራለን፡፡ በጋራ ጠንክረን እንሰራለን፡፡
ስለ ቻምፒዮንነት ፉክክሩ
ተስተካካይ ጨዋታዎች ይቀሩናል፡፡ ስለዚህ ከፉክክሩ አልወጣንም፡፡ እስከመጨረሻው ድረስ እንፎካከራለን፡፡